1 ሳሙኤል 25:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም ለበጎች ሸላቾቼ ያረድኳቸውን እንስሶች አንሥቼ ከወዴት እንደ መጡ ለማላውቃቸው ሰዎች የምሰጥበት ምክንያት የለም!” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም በጎቼን ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድሁትን ፍሪዳ ከየት እንደ መጡ ለማይታወቁ ሰዎች የምሰጠውስ ለምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም በጎቼን ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድሁትን ፍሪዳ ከየት እንደመጡ ለማይታወቁ ሰዎች የምሰጠውስ ለምንድን ነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራዬንና የወይን ጠጄን፥ ለሸላቾቼም ያረድሁትን ሥጋ ወስጄ ከወዴት እንደ ሆኑ ለማላውቃቸው ሰዎች እሰጣለሁን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራዬንና የወይን ጠጄን ለሸላቾቼም ያረድሁትን ሥጋ ወስጄ ከወዴት እንደ ሆኑ ለማላውቃቸው ሰዎች እሰጣለሁን? ብሎ መለሰላቸው። |
ከዚህ በኋላ ጌዴዎን ወደ ሱኮት ሰዎች መጥቶ “ ‘ዜባሕንና ጻልሙናዕን ገና አልማረክህም፤ ታዲያ አሁን በረሀብ ለደከሙት ወታደሮችህ ምግብ የምንሰጠው ለምንድን ነው?’ ብላችሁ አሹፋችሁብኝ ነበር፤ አሁን ግን ዜባሕና ጻልሙናዕ እነሆ በእጄ ይገኛሉ!” አላቸው።
ጌዴዎን ወደ ጵኑኤልም ሄዶ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ ነገር ግን የጵኑኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ተመሳሳይ መልስ ሰጡት።
‘ክፉ ነገርን የሚያደርጉ ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው’ የተባለውን ጥንታዊ አነጋገር ታውቃለህ፤ ስለዚህም እኔ በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አልፈልግም።
በጎችህንም እንደምታሸልት ሰምቶአል፤ እረኞችህ ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜም ሁሉ ምንም ዐይነት ጒዳት እንዳላደረስንባቸው እንድታውቅ ይፈልጋል፤ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ከመንጋቸው አንድ እንኳ አልተወሰደባቸውም፤