ይሁዳም ዕቃዎቹ የማን እንደ ሆኑ ዐውቆ “ከልጄ ከሴላ ጋር ስላላጋባኋት እርስዋ ከእኔ ይልቅ ትክክለኛ ሆና ተገኘች” አለ፤ ወደ እርስዋም ዳግመኛ አልገባም።
1 ሳሙኤል 24:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእጅህ ቢጥለኝም እንኳ አንተ አልገደልከኝምና ለእኔ በጎ አድራጊ መሆንህንም ዛሬ አስመስክረሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያደረግህልኝን በጎ ነገር ይኸው ነግረኸኛል፤ እግዚአብሔር እኔን በእጅህ ጥሎኝ ነበር፤ አንተ ግን አልገደልኸኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፤ “ክፉ ሳደርግብህ፥ በጎ መልሰህልኛልና፥ አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን አለው፥ “እኔ ክፉ በመለስሁልህ ፋንታ በጎ መልሰህልኛልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ አልገደልኸኝምና ለእኔ መልካም እንዳደረግህልኝ አንተ ዛሬ አሳየኸኝ። |
ይሁዳም ዕቃዎቹ የማን እንደ ሆኑ ዐውቆ “ከልጄ ከሴላ ጋር ስላላጋባኋት እርስዋ ከእኔ ይልቅ ትክክለኛ ሆና ተገኘች” አለ፤ ወደ እርስዋም ዳግመኛ አልገባም።
ዳዊትም “የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎችስ ተከታዮቼንና እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡን ይሆን?” ሲል እንደገና ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል” ሲል መለሰ።
ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቀዒላ መምጣቱ በተነገረው ጊዜ “እግዚአብሔር እርሱን በእጄ ሊጥልልኝ ነው፤ ዳዊት የግንብ ቅጽርና የተመሸጉ የቅጽር በሮች ወዳሉአት ከተማ በመዝለቁ ራሱን በወጥመድ ውስጥ አስገብቶአል” አለ።
ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤
ታማኞች ለሆኑ ለደጋግ ሰዎች የመልካም ሥራቸውን ዋጋ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ ጥሎልኝ ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔር መርጦ ያነገሠህን አንተን ልጐዳ አልፈለግሁም።
አቢሳም ዳዊትን “እግዚአብሔር በዛሬው ምሽት ጠላትህን በእጅህ ጥሎልሃል፤ ስለዚህ አሁን የገዛ ጦሩን አንሥቼ ልውጋውና ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ አንድ ምት ብቻ ስለሚበቃው ድጋሚ አያስፈልገውም!” አለው።