1 ሳሙኤል 23:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያን ቦታ ስም ሐማለኮዝ ብለው ጠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፥ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “የመለያያ ዓለት” ብለው ጠሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድን ትቶ ተመለሰ። ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመለያየት ዓለት ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድ ትቶ ተመለስ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚህ ስፍራ ስም የማምለጥ ዓለት ተባለ። |
ሳኦልና ወታደሮቹም ዳዊትን ለማሳደድ ወጥተው ሄዱ፤ ዳዊትም ይህን ስላወቀ በማዖን ምድረ በዳ አለት ወደበዛበት አንድ ኮረብታ አልፎ በዚያ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ ዳዊትን የመከታተል ተግባሩን ቀጠለ፤
ይህ በዚህ እንዳለ ወዲያውኑ አንድ መልእክተኛ ደርሶ ሳኦልን “ፍልስጥኤማውያን አገሪቱን በመውረር ላይ ናቸውና አሁኑኑ ፈጥነህ ተመልሰህ ና!” አለው።
ስለዚህም ሳኦል በእስራኤል ምርጥ የሆኑትን ሦስት ሺህ ወታደሮች በማስከተል “የሜዳ ፍየሎች አለት” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ዳዊትን አሳዶ ለመያዝ ሄደ፤