La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 23:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም እነርሱ ሳኦል ከመሄዱ በፊት ወደ ዚፍ ተመለሱ፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ በኩል በሚገኘው በማዖን በረሓ ነበሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሰዎቹ ለመሄድ ተነሥተው ከሳኦል በፊት ወደ ዚፍ ሄዱ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተ ደቡብ በዓረባ ውስጥ ባለው በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰዎቹም ሳኦል ከመሄዱ በፊት ወደ ዚፍ ተመለሱ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተ ደቡብ በዓረባ ውስጥ ባለው በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዚፍ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከሳ​ኦል በፊት ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ግን በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በኩል በዓ​ረባ በማ​ዖን ምድረ በዳ ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነዚያም ተነሥተው ከሳኦል በፊት ወደዚፍ ሄዱ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ግን በየሴሞን ደቡብ በኩል በዓረባ በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 23:24
4 Referencias Cruzadas  

ከእነዚህም ሌላ ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥


የሚሸሸግባቸውን ስፍራዎች በትክክል አግኙ፤ ያገኛችሁትንም ማስረጃ ወዲያው ይዛችሁልኝ ኑ፤ ከዚያም በኋላ እኔ አብሬአችሁ እሄዳለሁ፤ አሁንም በዚያው ግዛት ውስጥ የሚኖር ከሆነ መላውን የይሁዳ ግዛት ማሰስ ቢያስፈልገኝም እንኳ እርሱን በማደን እይዘዋለሁ።”


ሳኦልና ወታደሮቹም ዳዊትን ለማሳደድ ወጥተው ሄዱ፤ ዳዊትም ይህን ስላወቀ በማዖን ምድረ በዳ አለት ወደበዛበት አንድ ኮረብታ አልፎ በዚያ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ ዳዊትን የመከታተል ተግባሩን ቀጠለ፤


በዚያም ቤተሰቡ ከካሌብ ጐሣ የሆነ ናባል ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የማዖን ተወላጅ ሲሆን በቀርሜሎስ ከተማ አጠገብ የእርሻ መሬት ነበረው፤ ታላቅ ባለጸጋ ከመሆኑም የተነሣ ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ ሚስቱ አቢጌልም እጅግ የተዋበች አስተዋይ ሴት ስትሆን እርሱ ግን መልካም ጠባይ የጐደለው ባለጌ ሰው ነበር። ናባል በቀርሜሎስ በጎቹን ያሸልት ነበር፤