1 ሳሙኤል 20:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም በቊጣ ከማእዱ ላይ ተነሣ፤ በዚያ ቀን ማለትም አዲስ ጨረቃ በታየችበት በዓል በሁለተኛ ቀን ምንም ምግብ አልበላም፤ ሳኦል ዳዊትን በማዋረዱ ምክንያት ስለ ዳዊት ሁኔታ ዮናታን በብርቱ አዝኖ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም በታላቅ ቍጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም በታላቅ ቁጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱ በእርሱ ላይ ክፉ ነገርን ሊያደርግ ስለ ቈረጠ ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቈጥቶ ከማዕዱ ተነሣ፤ በመባቻውም በሁለተኛው ቀን ግብር አልበላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱ ዳዊትን ስላሳፈረው ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቆጥቶ ከሰደቃው ተነሣ፥ በመባቻውም በሁለተኛ ቀን ግብር አልበላም። |
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
ከዚህም የተነሣ ዮናታንን ለመግደል የያዘውን ጦር ወረወረበት፤ ስለዚህም ዮናታን አባቱ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቊርጥ ውሳኔ ማድረጉን አረጋገጠ፤