ስለዚህ ብዙ ኰርማዎችን፥ የሰቡ ወይፈኖችንና በጎችን መሥዋዕት አቅርቦአል፤ በበዓሉም ላይ እንዲገኙለት የንጉሡን ልጆች ካህኑን አብያታርንና የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዞአቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም።
1 ሳሙኤል 2:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በወጣትነት ዕድሜአቸው በሰይፍ ያልቃሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመሠዊያዬ የማላስወግዳቸው ዘሮችህ በሕይወት የሚተርፉትም ዐይኖችህን በእንባ ለማፍዘዝ፣ ልብህን በሐዘን ለማደንዘዝ ብቻ ነው፣ ሌሎቹ ዘሮችህ ግን በሙሉ በለጋነታቸው በዐጭር ይቀጫሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በሰዎች ሰይፍ ያልቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐይኖቹ የሚፈጽም በነፍሱም የሚተጋ ሰውን ከመሠዊያዬ አላጠፋም። ከቤትህ የሚቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐልማሶች ሰይፍ ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመሠዊያዬ ያልተቆረጠ ልጅህ ቢገኝ ዓይንህን ያፈዝዘዋል፥ ነፍስህንም ያሳዝናል ከቤትህም የሚወለዱ ሰዎች ሁሉ በጎልማስነት ይሞታሉ። |
ስለዚህ ብዙ ኰርማዎችን፥ የሰቡ ወይፈኖችንና በጎችን መሥዋዕት አቅርቦአል፤ በበዓሉም ላይ እንዲገኙለት የንጉሡን ልጆች ካህኑን አብያታርንና የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዞአቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም።
የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
እነሆ እኔ በምመለክበት ቦታ ብዙ ችግር ታያለህ፤ በእስራኤል ዘንድ በጎ ነገር የሚደረግ ቢሆንም ከአንተ ቤተሰብ መካከል ማንም ረጅም ዕድሜ የሚኖረው አይገኝም።
ስለዚህም ሳኦል ዶይቅን “አንተው ግደላቸው!” አለው፤ ኤዶማዊው ዶይቅም ተነሥቶ ሁሉንም ገደለ፤ በዚያኑ ቀን የፈጃቸው ኤፉድ የሚለብሱ ካህናት ብዛት ሰማኒያ አምስት ነበር፤