1 ሳሙኤል 2:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትእዛዜ መሠረት የሚቀርብልኝን መሥዋዕትና ቊርባን ለምን ታዋርዳላችሁ? ልጆችህ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ምርጥ የሆነውን እየወሰዱ በመብላት ይወፍሩ ዘንድ እነርሱን ከእኔ ይበልጥ የምታከብራቸው ለምንድነው?’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝሁትን መሥዋዕትና ቍርባን የናቃችሁ ለምንድን ነው? አንተና ልጆችህ ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቍርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር ከእኔ ይልቅ ልጆችህን የምታከብራቸው ስለ ምንድን ነው?’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማደሪያዬ እንዲያቀርቡት ያዘዝሁትን መሥዋዕቴንና ቁርባኔን ስለምን ረገጣችሁ? ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቁርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር፥ ከእኔ ይልቅ ለልጆችህ ስለምን ክብር ሰጠህ?’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሥዋዕቴ ላይና በዕጣኔ ላይ ስለ ምን በክፉ ዐይን ተመለከትህ? የእስራኤል ልጆች በፊቴ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ሁሉ በቀዳምያቱ ስለ አከበርሁህ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን መረጥህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማደሪያዬ ያቀርቡት ዘንድ ያዘዝሁትን መሥዋዕቴንና ቍርባኔን ስለ ምን ረገጣችሁ? እንድትወፍሩም የሕዝቤን የእስራኤልን ቍርባን ሁሉ መጀመሪያ በመብላታችሁ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርህ? |
እፍኝ ገብስ እና ቊራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ ሐሰትን ለሚያዳምጡ ለሕዝቤ ሐሰትን እየተናገራችሁ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች እንዲኖሩ በማድረግ ስሜ በሕዝቤ ዘንድ እንዲሰደብ አድርጋችኋል።”
እኔ ልዑል እግዚአብሔር የበጎቹን እረኞች እቃወማለሁ፤ በጎቹን ከእረኞች እጅ ወስጄ እንዳያሰማሩአቸው አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እረኞቹ ራሳቸውን አይመግቡም፤ ለእነርሱም ምግብ እንዳይሆኑ በጎቼን ከእነርሱ አፍ አስጥላለሁ።
“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ጠባቂዎች ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ሁሉ በትንቢት እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘መንጋውን መንከባከብና መጠበቅ ትታችሁ ራሳችሁን የምትጠብቁ እናንተ የእስራኤል እረኞች ወዮላችሁ!
“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።
እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ይላል፦ “ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን ‘ሰላም ይወርድላችኋል’ እያሉ ይሰብካሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ‘ጦርነት ይመጣባችኋል’ እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፤
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም።
የእነርሱንም ደቀ መዛሙርት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ወደ ኢየሱስ ልከው፥ “መምህር ሆይ! አንተ እውነተኛ መሆንህንና የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ሰውንም በመፍራት የምታደርገው ነገር የለም፤ ለሰውም አታዳላም” ካሉት በኋላ፥ እንዲህ ብለው ጠየቁት።
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።