La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 2:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዔሊም ሕልቃናን ከሚስቱ ከሐና ጋር በሚመርቅበት ጊዜ፥ ሕልቃናን “ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጋችሁ በሰጣችሁት በዚህ ልጅ ፈንታ ከዚህቹ ሴት ሌሎችን ልጆች ይስጥህ!” ይለው ነበር። ከዚያን በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዔሊም፣ “በጸሎት ባገኘችውና ለእግዚአብሔር በሰጠችው ልጅ ምትክ እግዚአብሔር ከዚህችው ሴት ዘር ይስጥህ” እያለ ሕልቃናንና ሚስቱን ይመርቃቸው ነበር፤ ከዚያ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ “ለጌታ ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት ጌታ ዘር ይስጥህ” ብሎ ባረካቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዔሊም ሕል​ቃ​ና​ንና ሚስ​ቱን ባረ​ካ​ቸው፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ባ​ኸው ስጦታ ፈንታ ከዚ​ህች ሴት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር ይስ​ጥህ” አለው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ ለእግዚአብሔር ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት እግዚአብሔር ዘር ይስጥህ ብሎ ባረካቸው፥ እነርሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 2:20
9 Referencias Cruzadas  

እንዲህ ብሎም አብራምን ባረከው፤ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ!


ታዲያ እግዚአብሔር እናንተና ሚስቶቻችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ እንዲኖራችሁ አድርጎ አልነበረምን? በዚህስ የእርሱ ዓላማ ምን ነበር? ዋና ዓላማው የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሆኑ ልጆችን እንድትወልዱ በመፈለግ ነበር፤ ስለዚህ ከእናንተ እያንዳንዱ ለሚስቱ የገባውን ቃል ኪዳን አያፍርስ።


ስምዖን ከባረካቸው በኋላ በተለይ የሕፃኑን እናት ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ! ይህ ሕፃን በእስራኤል ውስጥ ለብዙዎቹ የመጥፋት፥ ለብዙዎቹ ግን የመዳን ምክንያት ይሆናል፤ እርሱም ብዙዎች የማይቀበሉት ምልክት ይሆናል።


እግዚአብሔር ላደረግሽው በጎ ነገር ዋጋሽን ይክፈልሽ! የእርሱን ጥበቃ ተማምነሽ የመጣሽው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ዋጋሽን የተትረፈረፈ ያድርገው!”


በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤


ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።”