1 ሳሙኤል 17:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትሩን አንሥቶ፥ ከወንዝ ዳር አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በመልቀም በእረኝነት ኮረጆው ከተተ፤ ወንጭፉንም ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ፤ ዐምስት ድቡልቡል ድንጋዮች ከወንዝ መርጦ በእረኛ ኰረጆው ከጨመረ በኋላ፣ ወንጭፉን በእጁ ይዞ፣ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ፤ አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች ከወንዝ መርጦ በእረኛ ኮረጆው ከጨመረ በኋላ፥ ወንጭፉን በእጁ ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በትሩን በእጁ ያዘ፤ ከወንዝም አምስት ድብልብል ድንጋዮችን መረጠ፤ በእረኛ ኮሮጆውም በኪሱ ከተታቸው፤ ወንጭፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍልስጥኤማዊውም ቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትሩንም በእጁ ወሰደ፥ ከወንዝም አምስት ድብልብል ድንጋዮችን መረጠ፥ በእረኛ ኮረጆውም በኪሱ ከተታቸው፥ ወንጭፍም በእጁ ነበረ፥ ወደ ፍልስጥኤማዊውም ቀረበ። |
ከእነዚያም መካከል የተመረጡ ሰባት መቶ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ድንጋይ የሚወነጭፉና ሌላው ቀርቶ አንዲት ጠጒርን እንኳ የማይስቱ ነበሩ።
ከዚያም ቀጥሎ የነበረው መሪ የዐናት ልጅ ሻምጋር ነበር፤ እርሱም ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ ቀንድ በመግደል፥ የእስራኤልን ሕዝብ አዳነ።
ዳዊትም ይህን ዐይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመሄድ ሲነሣ መራመድ አልቻለም፤ ስለዚህ ዳዊት ሳኦልን፦ “ያልተለማመድኩት ነገር ስለ ሆነ ይህን ሁሉ ልብስ ለብሼ መዋጋት አልችልም፤” አለ፤ ስለዚህም ያንን ሁሉ አወለቀ፤