Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 20:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከእነዚያም መካከል የተመረጡ ሰባት መቶ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ድንጋይ የሚወነጭፉና ሌላው ቀርቶ አንዲት ጠጒርን እንኳ የማይስቱ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በእነዚህም ሁሉ መካከል እያንዳንዳቸው ድንጋይ ወንጭፈው ጠጕር እንኳ የማይስቱ ሰባት መቶ ምርጥ ግራኞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በእነዚህም ሁሉ መካከል እያንዳንዳቸው ድንጋይ ወንጭፈው ጠጉር እንኳ የማይስቱ ሰባት መቶ ምርጥ ግራኞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ነ​ዚ​ያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ፥ ሁለ​ቱም እጆ​ቻ​ቸው ቀኝ የሆ​ኑ​ላ​ቸው ሰዎች ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ድን​ጋይ ይወ​ነ​ጭፉ ነበር፤ አን​ዲት ጠጕ​ርስ እንኳ አይ​ስ​ቱም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእነዚያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተመረጡ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፥ እነዚህም ሁሉ ድንጋይ ይወነጭፉ ነበር፥ አንዲት ጠጉርስ እንኳ አይስቱም።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 20:16
7 Referencias Cruzadas  

እነርሱም ከብንያም ነገድ ስለ ነበሩ የሳኦል ዘመዶች ነበሩ፤ እነርሱ በቀኝና በግራ እጃቸው ፍላጻ የመወርወርና ድንጋይ የመወንጨፍ ችሎታ ያላቸው ነበሩ፤


ዖዝያም ለመላው ሠራዊቱ ጋሻና ጦር፥ የራስ ቊርና የደረት ጥሩርን፥ ቀስትና ፍላጻን፥ ወንጭፍና የሚወነጨፉ ድንጋዮችን አዘጋጅቶለት ነበር፤


እስራኤላውያን የብንያምን ነገድ ሳይጨምሩ ብዛቱ አራት መቶ ሺህ መሣሪያ የታጠቀ ሠራዊት አሰለፉ።


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።


በትሩን አንሥቶ፥ ከወንዝ ዳር አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በመልቀም በእረኝነት ኮረጆው ከተተ፤ ወንጭፉንም ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ።


ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios