እግዚአብሔርም፥ “በማሕፀንሽ ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።
1 ሳሙኤል 17:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የሁሉ ታናሽ ሲሆን፥ ሦስት ታላላቅ ወንድሞቹ ሳኦልን ተከትለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር። ሦስቱ ታላላቅ ወንድሞቹ ሳኦልን ተከትለው ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር። ሦስቱ ታላላቅ ወንድሞቹ ሳኦልን ተከትለው ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም የሁሉ ታናሽ ነበረ፤ ሦስቱም ታላላቆቹ ሳኦልን ተከትለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊት የሁሉ ታናሽ ነበረ፥ ሦስቱም ታላላቆች ሳኦልን ተከትለው ነበር። |
እግዚአብሔርም፥ “በማሕፀንሽ ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።
“ታዲያ ሌሎች ልጆች የሉህምን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም “የሁሉ ታናሽ የሆነ አንድ ልጅ አለ፤ እርሱ ግን ወደ በግ እረኝነት ሄዶአል” ሲል መለሰለት። ሳሙኤልም “እርሱን አስጠርተህ አምጣው፤ እርሱ ሳይመጣ መሥዋዕት አናቀርብም” አለው።