1 ሳሙኤል 14:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቱም አሒኖዓም ተብላ የምትጠራ የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር ተብሎ የሚጠራው የአጐቱ የኔር ልጅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ሚስት አኪናሆም የምትባል የአኪማአስ ልጅ ነበረች፤ የሰራዊቱም አዛዥ አበኔር የሚባል የአጎቱ የኔር ልጅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ሚስት አሒኖዓም የምትባል የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር የሚባል የሳኦል አጎት የኔር ልጅ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማአስ ልጅ አኪናሆም ነበረ፥ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበረ። |
አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።
ሸሎሚትና ዘመዶቹ ለቤተ መቅደስ ሥራ ለተለዩ ነገሮች ሁሉ፥ በነቢዩ ሳሙኤል፥ በንጉሥ ሳኦል፥ በኔር ልጅ አበኔርና በጸሩያ ልጅ ኢዮአብ ላቀረቡአቸው ስጦታዎች ጭምር ኀላፊዎች ነበሩ።
የሳኦል አጐት ሳኦልንና አገልጋዩን አይቶ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ሳኦልም “አህዮች ልንፈልግ ሄደን ልናገኛቸው ስላልቻልን ሳሙኤልን ለመጠየቅ ጎራ ብለን ነበር” ሲል መለሰለት።
ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።
ከዚያም በፍጥነት ተነሥቶ በመሄድ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የሚተኙበትን ቦታ አረጋገጠ፤ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ ወታደሮቹ በዙሪያው ይገኙ ነበር።