እስከ ሰሜን ንፍታሌም ድረስ ባሉ በምናሴ፥ በኤፍሬምና በስምዖን ግዛቶች በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በተደመሰሱት አካባቢዎቻቸው ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸመ።
1 ሳሙኤል 13:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እስራኤላውያን ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፥ መጥረቢያቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን መውረድ ነበረባቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፣ ጠገራቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፥ መጥረቢያቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ሁሉ ማረሻውንና ማጭዱን፥ መጥረቢያውንና መቈፈሪያውን ይስሉ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ የማረሻውን ጫፍና ማጭዱን መጥረቢያውንና መቆፈሪያውን ይስል ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርድ ነበር። |
እስከ ሰሜን ንፍታሌም ድረስ ባሉ በምናሴ፥ በኤፍሬምና በስምዖን ግዛቶች በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በተደመሰሱት አካባቢዎቻቸው ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸመ።
ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤
መጥረቢያ ለማሳልና የበሬ መንጃ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ አራት ግራም ያኽል የሚመዝን ጥሬ ብር ነበር፤ ማረሻና ዶማ ለማሾልም የሚከፈለው ዋጋ የዚሁ እጥፍ ነበር።