17 ብረት ብረትን እንደሚስል ሰውም እርስ በእርሱ አንዱ ከሌላው ይማራል።
17 ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።
17 ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን እንዲሁ።
በፍቅርና በመልካም ሥራ ነቅተን እንድንኖር አንዱ ሌላውን ያሳስበው፤
ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል።
የሳኦል ልጅ ዮናታንም እዚያው ድረስ ወደ ዳዊት ሄዶ እግዚአብሔር በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቀው መሆኑን በመግለጥ እንዲህ እያለ አበረታታው፤
አንተም የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር በመሆን ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል።
ወንድሞቼ ሆይ! ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን እንዳገኛችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ።
እንግዲህ ስለ ጌታችን ለመመስከር አትፈር፤ ስለ እርሱ በታሰርኩት በእኔም አትፈር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሚሰጥህ ኀይል ስለ ወንጌል ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል።
ይህም በደረሰባችሁ መከራ እንዳትናወጡ ያደርጋችኋል፤ ይህ መከራ ለእኛ የተወሰነልን ዕጣ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
ይህን መከራ የምቀበለውም በዚህ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ማንን እንዳመንኩ ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የተሰጠኝንም ዐደራ እስከዚያ ቀን ድረስ መጠበቅ እንደምችል ተረድቼአለሁ።
የአንተን ሥልጣን የሚቃወምና ትእዛዝህን ሁሉ የማይፈጽም ቢኖር በሞት ይቀጣ፤ ብቻ አንተ በርታ!”
ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ “የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ እኛን በመፍራት ሐሞታቸው ስለ ፈሰሰ በእውነት እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ ለእኛ አሳልፎ ሰጥቶአል።”
ነፋስን ለማቆም ዘይትንም በእጅ ጨብጦ ለመያዝ እንደማይቻል ሁሉ እርስዋንም ዝም ማሰኘት አይቻልም።
የበለስን ዛፍ ተንከባክበህ ብትጠብቅ የበለስ ፍሬ ትበላለህ፤ አሳዳሪውን የሚንከባከብ አገልጋይም ይከበራል።
ቊጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ግልፍተኛም ብዙ በደልን ይፈጽማል።
ማርያም ይህን በሰማች ጊዜ በፍጥነት ተነሥታ ወደ እርሱ ሄደች።