ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
1 ሳሙኤል 13:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን፣ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር፣ በመላው የእስራኤል ምድር የእጅ ጥበብ ባለሙያ አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም፥ “ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ” ብለው ነበርና በእስራኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም፦ ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ብለው ነበርና በእስርኤል ምድር ሁሉ ብረተ ሠሪ አልተገኘም። |
ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
“እነሆ፥ በወናፉ ፍሙን የሚያናፋውን ብረት አቅላጭ የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ እርሱም መሣሪያውን የሚሠራው ለየተሠራለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ነው፤ ያጠፋ ዘንድ አጥፊውን የፈጠርኩ እኔ ነኝ።
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ፍሬ ቅርጫቶችን አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮአቄም ልጅ የሆነውን የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳ መሪዎች፥ ከእጅ ጥበብ ባለሞያዎችና ከሌሎችም ብልኀተኞች ሠራተኞች ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን አስሮ ከወሰደ በኋላ ነው።
ደብዳቤውንም የጻፍኩት ንጉሡ ኢኮንያን፥ እቴጌይቱ እናቱና የቅርብ አገልጋዮቹ፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መሪዎች፥ የእጅ ጥበብ ሠራተኞችና ሙያተኞች ሁሉ ተማርከው ከተወሰዱ በኋላ ነው፤
እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም!