ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
1 ሳሙኤል 12:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ ይህን የመሰለ ክፉ ነገር ያደረጋችኹ ብትሆኑ እንኳ በሙሉ ልባችሁ እርሱን አገልግሉት እንጂ ፊታችሁን ከእግዚአብሔር ወደ ሌላ አትመልሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አትፍሩ፤ ይህን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፤ ሆኖም እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አትፍሩ፤ ይህን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፤ ሆኖም ጌታን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ ጌታን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ አላቸው፥ “አትፍሩ፤ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ፦ አትፍሩ፥ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። |
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
በማግስቱም ሙሴ ለእስራኤላውያን “አስከፊ የሆነ ታላቅ በደል ሠርታችኋል፤ ነገር ግን እነሆ አሁንም እንደገና እግዚአብሔር ወደሚገለጥበት ተራራ እወጣለሁ፤ ምናልባት ስለ ኃጢአታችሁ ይቅርታ አስገኝላችሁ ይሆናል” አለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ እርስዋም ከእርሱ ተለይታ ሌላ ወንድ ካገባች በኋላ እንደገና መልሶ ሊያገባት ይችላልን? ይህ ቢደረግማ ፈጽሞ ምድርን የሚያረክስ ይሆናል። እስራኤል ሆይ! አንቺ ግን ብዙ ጣዖቶችን ወደሽ ነበር፤ አሁን ደግሞ እንደገና ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽ።
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ‘እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ’ ብዬ በሰጠሁት የተስፋ ቃል መሠረት አሁንም መንፈሴ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነ አይዞአችሁ አትፍሩ” ብሎ ነገራቸው።
“እንግዲህ እስራኤል ሆይ! እግዚአብሔር አምላክህን እንድትፈራው፥ በመንገዱ ሁሉ እንድትሄድ፥ እንድትወደው በሙሉ ልብህና በሙሉ ሐሳብህ እንድታመልከው፥ ለደኅንነትህ ሲባል እኔ ዛሬ የማዝህን የእግዚአብሔር አምላክህን ትእዛዝና ድንጋጌ እንድትጠብቅ ነው እንጂ እርሱ ሌላ ከአንተ ምን ይፈልጋል?
እኔ ከሞትሁ በኋላ ካዘዝኳቸው ትእዛዝ በመውጣት የርኲሰትን ሥራ እንደሚፈጽሙ ዐውቃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ በመሥራት ስለሚያስቈጡት መቅሠፍት ያመጣባቸዋል።”
ስለዚህም በኦሪት ሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዞች ሁሉ ለመጠበቅ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ከእነርሱም ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ አትበሉ።
መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።
ሳሙኤልንም እንዲህ አሉት፤ “እንዳንሞት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ ሌላውን ኃጢአት ሁሉ ከመሥራት አልፈን ንጉሥ እንዲያነግሥልን በመጠየቃችን በደለኞች መሆናችንን አሁን ተገንዝበናል።”