ዮዳሄ፥ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ።
1 ሳሙኤል 10:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ለሕዝቡ፥ ለአንድ ንጉሥ ሊደረግለት የሚገባውን ሥርዓት አስረዳቸው፤ ያንንም በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡን ሁሉ ወደየቤቱ አሰናበተ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ወግና ሥርዐት ለሕዝቡ ገልጾ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ተግባርና ሥርዓት ለሕዝቡ ገልጦ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በጌታ ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም የንጉሡን ሥርዐት ነገራቸው፤ በመጽሐፍም ጻፈው፤ በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እየቤታቸው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም የመንግሥቱን ወግ ነገረ፥ በመጽሐፍም ጻፈው በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው። |
ዮዳሄ፥ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ።
“የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ይህን መጽሐፍ ወስዳችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ምስክር ይሆንባቸዋል።
እግዚአብሔርን በመፍራትና በመልካም ጠባይ እየተመራን በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር በተለይ ለነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ።
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ የሚሉህን ተቀበል፤ ነገር ግን ንጉሦቻቸው ወደ ፊት በእነርሱ ላይ የሚፈጽሙባቸውን ነገር ሁሉ በመግለጥ በብርቱ አስጠንቅቃቸው።”