ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ፦ “ከእኔ ጋር ሆነህ በምሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፥ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፥
1 ሳሙኤል 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ፦ “ከእኔ ጋር ሆነህ በምሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፥ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፥
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ፤ ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም መጒደል ጀመረ።
“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ተስሎ ሲፈጸምለት፥ ያ የተሳለው ስለት ሰውን ለመስጠት ከሆነ የመዋጀት ዋጋው እንደ ገመትከው ሆኖ እንደሚከተለው ይሁን፦
በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን “ይህን ሕዝብ ድል እንድንነሣው ብትረዳን፥ እነርሱንም ሆኑ ከተሞቻቸውን ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ አድርገን በፍጹም እንደመስሳቸዋለን” በማለት ለእግዚአብሔር ተሳሉ።
ካህኑም አንዱን ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት፥ ሌላውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ናዝራዊው ሬሳ በመንካቱ ስለ ረከሰ ያስተሰርይለታል፤ በዚያኑ ቀን ናዝራዊው ጠጒሩን እንደገና ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ያደርገዋል።
“ስእለት ተስሎ በናዝራዊነት እስካለ ድረስ ራሱን ምላጭ አይንካው፤ የናዝራዊነት ጊዜው እስኪፈጸም ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ (የተቀደሰ) ይሆናል፤ የራሱንም ጠጒር ያሳድጋል።
በእርግጥ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የራስ ጠጒሩን ፈጽሞ አይላጭ፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።”
በማግስቱም ሕልቃናና ቤተሰቡ በማለዳ ተነሥተው ለእግዚአብሔር ከሰገዱ በኋላ በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ሄዱ፤ ሕልቃናም ከሚስቱ ከሐና ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እግዚአብሔርም አስታወሳት፤
“ልጄ ጡት በሚተውበት ጊዜ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ወደሚኖርበት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወዲያውኑ እወስደዋለሁ” ብላ ለባልዋ ነግራው ስለ ነበር ሐና በዚህ ጊዜ አብራ አልወጣችም፤
እኔም ደግሞ እርሱን ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ እንዲሆን አድርጌአለሁ፤ ስለዚህም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” ከዚያም በኋላ በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
ዔሊም ሕልቃናን ከሚስቱ ከሐና ጋር በሚመርቅበት ጊዜ፥ ሕልቃናን “ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጋችሁ በሰጣችሁት በዚህ ልጅ ፈንታ ከዚህቹ ሴት ሌሎችን ልጆች ይስጥህ!” ይለው ነበር። ከዚያን በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።