1 ነገሥት 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ ከተሞች ምንድን ናቸው?” አለ፤ እነዚህንም “ከቡል ምድር” አላቸው፤ እስከ ዛሬም በዚሁ ስም ይጠራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለው፥ “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድን ናቸው?” እስከ ዛሬም ድረስ ወሰን ብሎ ጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድር ናቸው?” አለ። እስከ ዛሬም ድረስ የከቡል አገር ተብለው ተጠሩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤
ወደ ምሥራቅም ይታጠፍና ድንበሩ ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ነዒኤል በሚወስደው መንገድ ከዛብሎንና ከይፍታሕኤል ሸለቆ እየተዋሰነ ወደ ቤትዳጎን ይዘልቃል። በሰሜንም ወደ ካቡል፥