ሆኖም ከብር ለሚሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያ፥ ጐድጓዳ ወጭት፥ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርም ሆነ ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅድሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም።
1 ነገሥት 7:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦ የወርቅ መሠዊያ፣ የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወርቁን መሠዊያ፥ የገጹም ኅብስት የነበረበትን የወርቅ ገበታ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ አሠራ፤ የወርቁን መሠዊያ፥ የገጹም ኅብስት የነበረበትን የወርቅ ገበታ፥ |
ሆኖም ከብር ለሚሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያ፥ ጐድጓዳ ወጭት፥ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርም ሆነ ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅድሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም።
በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር በተናገረውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረው።
እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ የሚከተሉትን ዕቃዎች ከወርቅ አሠርቶአል፦ መሠዊያውና ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ ጠረጴዛ፥
እንዲሁም ዐሥር ጠረጴዛዎችን አሠርቶ በቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል ውስጥ አምስቱን በሰሜን፥ አምስቱን በደቡብ በኩል አኖራቸው፤ በተጨማሪም አንድ መቶ ማንቈርቈሪያዎችን ከወርቅ አሠራ።
በመግቢያው ክፍል በኩል በግራና በቀኝ ትይዩ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ በእነዚያም ጠረጴዛዎች ላይ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትና ለበደል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች ይታረድባቸው ነበር።
እንደዚሁም ለሚቃጠለው መሥዋዕት ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፥ ከፍታቸው አንድ ክንድ ነበር፤ እነርሱም ለሚቃጠለውና ለሌሎች መሥዋዕት የማረጃ ዕቃዎች ማስቀመጫነት የሚያገለግሉ ነበሩ።
በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ ፊት ለፊት፥ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ የሚመስል ነገር ይታይ ነበር፤ እርሱም እኩልነት ያለው አራት ማእዘን ሲሆን፥ እያንዳንዱ ማእዘን ሁለት ክንድ ነበር፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበር፤ የማእዘን መደገፊያ ምሰሶዎቹ፥ መሠረቱና ጐኖቹ ሁሉ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ ያም ሰው “ይህ በእግዚአብሔር ፊት የሚገኝ ጠረጴዛ ነው” አለኝ።
እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር እርሱም ሆነ አብረውት የነበሩት ሰዎች ሊበሉት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰ ኅብስት በላ።
የጌታን ጽዋ እየጠጣችሁ ደግሞ የአጋንንትን ጽዋ መጠጣት አትችሉም፤ የጌታ ማእድ ተካፋዮች ሆናችሁ ደግሞ የአጋንንትን ማእድ ተካፋይ መሆን አትችሉም፤