Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 7:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ከነሐስ የተሠራው ይህ ሁሉ ዕቃ እጅግ ብዙ ስለ ነበር፥ ሰሎሞን በሚዛን እንዲለካ አላደረገውም፤ ስለዚህ ክብደቱ ምን ያኽል እንደ ሆነ ተወስኖ አልታወቀም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ከነሐስ የተሠራው ይህ ሁሉ ዕቃ እጅግ ብዙ ስለ ነበር፥ ሰሎሞን በሚዛን እንዲለካ አላደረገውም፤ ስለዚህ ክብደቱ ምን ያኽል እንደሆነ ተወስኖ አልታወቀም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ሰሎሞንም ዕቃውን ሁሉ ሳያስመዝን አኖረ፤ የናሱም ሚዛን ከብዛቱ የተነሣ አይቆጠርም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 7:47
7 Referencias Cruzadas  

እነርሱም ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችን፥ መኰስተሪያዎችን፥ የዕጣን ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠሩ የቤተ መቅደሱ መገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰዱ።


ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ታላቁን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፥ በክብደታቸው ምክንያት ሊመዝኑአቸው አልቻሉም።


ስለ ቤተ መቅደሱ ሥራ የሆነ እንደሆን፥ በበኩሌ ለሕንጻ ሥራ የሚውል ሦስት ሺህ አራት መቶ ቶን ወርቅና ከሠላሳ አራት ሺህ ቶን በላይ የሚሆን ብር አከማችቼልሃለሁ፤ በተጨማሪም ስፍር ቊጥር የሌለው ነሐስና ብረት አዘጋጅቼልሃለሁ፤ እንዲሁም እንጨትና ድንጋይ አዘጋጅቼልሃለሁ፤ ይሁን እንጂ አንተም በተጨማሪ ማግኘት አለብህ፤


በወርቅ፥ በብር፥ በነሐስና በብረት ሥራ የታወቁ ልዩ ልዩ ሙያ ያላቸው ሰዎች አሉህ፤ እንግዲህ አሁን ሥራህን ጀምር፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን።”


ዳዊት ለቅጽር በሮቹ መሥሪያ የሚሆን ምስማርና ማጠፊያ የሚሠራበት ብዙ ብረት፥ እንዲሁም የክብደቱ ሚዛን እጅግ ብዙ የሆነ ነሐስ አዘጋጀ፤


በዚህ ዐይነት የተሠሩት ዕቃዎች እጅግ ብዙ ስለ ነበሩ እነርሱን ለማሠራት የተጠቀመበት ጠቅላላ የነሐስ ክብደት ምን ያኽል እንደ ሆነ ማንም ሊያውቅ አልቻለም።


እንዲሁም ሁለቱን ምሰሶዎች፥ አንዱን ገንዳ፥ ዐሥራ ሁለት በኰርማ ቅርጽ ከነሐስ የተሠሩትን የገንዳ ማስቀመጫዎች፥ ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ አሠርቶአቸው የነበሩትን ተሽከርካሪ መቆሚያዎችን ሁሉ ወሰደ። እነዚህ ዕቃዎች የተሠሩበት ነሐስ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሊመዘን አልተቻለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos