1 ነገሥት 6:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ስፋቱም ሃያ ክንድ፥ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ በጥሩም ወርቅ ለበጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅድስተ ቅዱሳንም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ስፋቱም ሃያ ክንድ ቁመቱም ሀያ ክንድ ነበረ፤ በጥሩ ወርቅም ለበጠው። |
ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም በወርቅ በተለበጠው ውስጠኛ ክፍል መግቢያ በር ክፈፉንም በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው።
ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ፥
የቤተ መቅደሱን ግድግዳዎች፥ የጣራውን ክፈፎች፥ መቃኖችና መዝጊያዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስሎች ቀረጸባቸው።
በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ ፊት ለፊት፥ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ የሚመስል ነገር ይታይ ነበር፤ እርሱም እኩልነት ያለው አራት ማእዘን ሲሆን፥ እያንዳንዱ ማእዘን ሁለት ክንድ ነበር፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበር፤ የማእዘን መደገፊያ ምሰሶዎቹ፥ መሠረቱና ጐኖቹ ሁሉ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ ያም ሰው “ይህ በእግዚአብሔር ፊት የሚገኝ ጠረጴዛ ነው” አለኝ።
ከመካከለኛው ክፍል ባሻገር ያለውን ውስጠኛ ክፍል ከማእዘን እስከ ማእዘን ሲለካ ርዝመቱ ኻያ ክንድ ወርዱም ኻያ ክንድ ሆነ፤ ከዚያም በኋላ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።