1 ነገሥት 22:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሶርያ ንጉሥ “በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ሠላሳ ሁለቱን የሠረገላ አዛዦች፣ “ከራሱ ከእስራኤል ንጉሥ በቀር ትንሽም ሆነ ትልቅ ከሌላ ከማንም ጋራ እንዳትዋጉ” ብሎ አዝዟቸው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሶርያ ንጉሥ “በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርያም ንጉሥ ሠላሳ ሁለቱን የሰረገሎች አለቆች፥ “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር፥ ታናሽ ቢሆን ወይም ታላቅ ከማናቸውም ጋር አትዋጉ” ብሎ አዝዞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶርያም ንጉሥ ሠላሳ ሁለቱን የሠረገሎች አለቆች “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር፥ ታናሽ ቢሆን ወይም ታላቅ ከማናቸውም ጋር አትግጠሙ፤” ብሎ አዝዞ ነበር። |
ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤
የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።
ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች የሆኑ ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ በመጠጥ ሰክረው በነበሩበት ጊዜ እኩለ ቀን ላይ የእስራኤል ሠራዊት ወጣ፤
የሶርያ ንጉሥም “የእስራኤል ንጉሥ አክዓብን ነጥላችሁ ግደሉ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ።
በዚህች ምድር የሚገኙ ሀብታሞችም ድኾችም ሁሉ ይሞታሉ፤ አልቅሶ የሚቀብራቸውም አያገኙም፤ ስለ እነርሱ ሐዘኑን ለመግለጥ ፊቱን የሚነጭም ሆነ ጠጒሩን የሚላጭ አይኖርም።