ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ይነፍስ፥ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፤ ንጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤
1 ነገሥት 21:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ ሬሳዋን በኢይዝራኤል ከተማ ውስጥ ውሾች ይበሉታል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር፣ ‘በኢይዝራኤል ቅጥር አጠገብ ውሾች ኤልዛቤልን ይበሏታል’ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሶርያም ንጉሥ ባርያዎች እንዲህ አሉት፦ “አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው፥ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፥ ነገር ግን በሜዳ ላይ ከእነርሱ ጋር ብንዋጋ በእርግጥ እንበረታባቸዋለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርያም ንጉሥ አገልጋዮች እንዲህ አሉት፥ “የእስራኤል አምላክ የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም፤ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ብንዋጋቸው ድል እናደርጋቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶርያም ንጉሥ ባሪያዎች እንዲህ አሉት፦ አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው፤ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ላይ ከእነርሱ ጋር ብንዋጋ በእርግጥ እንበረታባቸዋለን። |
ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ይነፍስ፥ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፤ ንጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤
በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ሁለንተናውን ለኃጢአት አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚምስል ማንም አልነበረም፤ ይህን ሁሉ ለማድረግ የተገደደው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፤
ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የእርስዋም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤’ ” ይህን ሁሉ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወጣቱ ነቢይ በሩን በመክፈት ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ።
እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤