ስለዚህም እስራኤላውያን ዳዊትን ከድተው ከሼባዕ ጋር ሄዱ፤ የይሁዳ ሕዝብ ግን ታማኝነታቸውን በማጽናት ከዮርዳኖስ እስከ ኢየሩሳሌም ዳዊትን ተከትለው ሄዱ።
1 ነገሥት 12:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባኤአቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረም የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮርብዓም መመለሱን እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ጉባኤያቸው በማስጠራት በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት። ለዳዊት ቤት በታማኝነት ጸንቶ የተገኘው የይሁዳ ቤት ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባኤአቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረም የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እስራኤል በሙሉ ኢዮርብዓም ከግብፅ እንደ ተመለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸንጎአቸው ጠሩት፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሡት። ከብቻው ከይሁዳና ከብንያም ነገድ በቀር የዳዊትን ቤት የተከተለ ማንም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም እንደ ተመለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸንጎአቸው ጠሩት፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሡት። ከብቻው ከይሁዳ ነገድ በቀር የዳዊትን ቤት የተከተለ አንድ ሰው አልነበረም። |
ስለዚህም እስራኤላውያን ዳዊትን ከድተው ከሼባዕ ጋር ሄዱ፤ የይሁዳ ሕዝብ ግን ታማኝነታቸውን በማጽናት ከዮርዳኖስ እስከ ኢየሩሳሌም ዳዊትን ተከትለው ሄዱ።
ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”
በሰሎሞን ላይ ያመፀው ሌላው ሰው በኤፍሬም ጸሬዳ ተብላ የምትጠራው ክፍል ተወላጅ የሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነው፤ እርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ ተብላ የምትጠራ ባልዋ የሞተባት ሴት ነበረች።
ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተዉ በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በሐሰትና በማታለል ከበውኛል፤ ይሁዳ ግን አሁንም እኔ በእግዚአብሔር በምመራው መንገድ ይሄዳል፤ ለእኔ ለቅዱሱም ታማኝ ነው።
“ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤ እኔን ሳይጠይቁ መሳፍንትን መርጠው ሾሙ፤ ከብራቸውና ከወርቃቸው ለገዛ ራሳቸው መጥፊያ የሆኑትን ጣዖቶችን ሠሩ።
ሳሙኤልም ሕዝቡን “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እነሆ ይህ ነው! ከእኛም መካከል እርሱን የሚስተካከለው የለም” አለ። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” አሉ።