1 ነገሥት 1:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነቢዩም መምጣት ለንጉሡ ተነገረው፤ ናታንም ወደ ውስጥ በመግባት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለንጉሡም፣ “ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ንጉሡ ፊት ቀርቦ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለንጉሡም፦ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፥ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግምባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለንጉሡም፥ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቶአል” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግንባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለንጉሡም “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቶአል፤” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግምባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ። |
እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር።