1 ነገሥት 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ማን መሆኑን እንድታስታውቀው በመጠባበቅ ላይ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ከአንተ ቀጥሎ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ ማን መቀመጥ እንዳለበት እንድታሳውቀው የእስራኤል ዐይን ሁሉ አንተን ይመለከታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል። |
ስለዚህ ብዙ ኰርማዎችን፥ የሰቡ ወይፈኖችንና በጎችን መሥዋዕት አቅርቦአል፤ በበዓሉም ላይ እንዲገኙለት የንጉሡን ልጆች ካህኑን አብያታርንና የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዞአቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም።
ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።
አምላካችን ሆይ! በእኛ ላይ አደጋ ሊጥሉ በብዛት የመጡትን እነዚህን ሠራዊት ሁሉ መቋቋም ስለማንችል አንተ ራስህ ፍረድባቸው፤ የአንተን ርዳታ ለማግኘት ዐይናችንን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር ሌላ ምንም ማድረግ እንደሚገባን አናውቅም።”
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አገልጋዮችና ገረዶች የአሳዳሪዎቻቸውን እጅ እንደሚጠባበቁ ሁሉ እኛም እስክትምረን ድረስ የአንተን ምሕረት ለማግኘት እንጠባበቃለን።
እነሆ፥ በኢያሱ ፊት ሰባት ቅርጽ ያለው አንድ ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም ላይ የጽሑፍ መግለጫ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም አገር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።