1 ዮሐንስ 2:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሙን የሚወድ ሁሉ በብርሃን ይኖራል፤ በእርሱም ሰውን የሚያሰናክል ነገር አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሙን የሚወድድ በብርሃን ይኖራል፤ በርሱም ዘንድ የመሰናከያ ምክንያት የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል፥ በእርሱም ዘንድ ማሰናከያ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ |
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በልቡ ውስጥ ሥር አልሰደደም፤ ስለዚህ በቃሉ ምክንያት አንዳች ችግር ወይም ስደት በደረሰበት ጊዜ ቶሎ ይሰናከላል።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሰዎች እንዲሰናከሉ በሚያደርጉት ነገሮች ምክንያት ለዓለም ወዮላት! መቼም የሚያሰናክሉ ነገሮች መምጣታቸው አይቀርም፤ ነገር ግን የመሰናከያው መምጫ ለሚሆነው ለዚያ ሰው ወዮለት!
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።