1 ቆሮንቶስ 9:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ደግሞ ወንጌልን የሚያስተምሩ ቀለባቸውን ከዚሁ ሥራቸው እንዲያገኙ ጌታ ደንግጎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ወንጌልን የሚሰብኩ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ከወንጌል እንዲቀበሉ ጌታ አዝዟል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚያበስሩ ከወንጌል ቀለባቸውን እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችንም እንዲሁ ወንጌልን ለሚያስተምሩ ሰዎች ለሕይወታቸው መተዳደሪያ በዚያው ወንጌልን በማስተማር ይሆን ዘንድ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል። |
ሌሎች ይህን ነገር ከእናንተ የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ ታዲያ፥ እኛ ከዚህ የሚበልጥ መብት እንዴት አይኖረንም? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይህን ማድረጋችንም የክርስቶስ የምሥራች ቃል ከመስፋፋት እንዳይገታ በማሰብ ሁሉን ነገር ታግሠን እንቻል ብለን ነው።
ወንጌላችንን ያበሠርንላችሁ በቃል ብቻ ሳይሆን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ ስለ ወንጌልም እውነት እርግጠኞች በመሆን ነው፤ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ ለእናንተ ስንል እንዴት እንደ ኖርን ታውቃላችሁ።