La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 15:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሁሉ በሥልጣኑ ሥር እስኪያደርግለት ድረስ ክርስቶስ መንገሥ ይገባዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጠላ​ቶቹ ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይነ​ግሥ ዘንድ አለ​ውና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 15:25
12 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።


እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።


‘እግዚአብሔር ለጌታዬ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ!’ አለው።


ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ፥ ‘እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ)፥ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤’ ብሎታል።


እንግዲህ ወደ ሰማይ የወጣው ዳዊት ባለመሆኑ ዳዊት ራሱ እንዲህ ሲል ተናግሮአል፤ ‘ጌታ ለጌታዬ (ለመሲሑ) ጠላቶችህን በሥልጣንህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ’ ብሎታል።


ሁሉንም ነገር በሥልጣኑ ሥር አድርጎ አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም ከሁሉ በላይ እንዲሆን ራስ አደረገው።


እግዚአብሔር ከመላእክቱ መካከል፥ “ጠላቶችህን ከሥልጣንህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ማንን ነው?


ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አደረግህለት።” ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ሲያደርግ፤ በሥልጣኑ ሥር ሳያደርግለት ያስቀረው ምንም ነገር የለም። ነገር ግን አሁን እንዳለ ሁሉ ነገር በእርሱ ሥልጣን ሥር እንደ ሆነ ገና አላየንም።