1 ቆሮንቶስ 15:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክርስቶስ አምነው የሞቱት ጠፍተዋል ማለት ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ከሆነ፣ በክርስቶስ ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስም ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲያስ በክርስቶስ አምነው የሞቱ ጠፍተዋላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲያስ በክርስቶስ ያንቀላፉት ደግሞ ጠፍተዋላ። |
የትእዛዝ ድምፅ፥ የመላእክት አለቃ ድምፅ፥ የእግዚአብሔር እምቢልታም ይሰማል፤ ጌታ ራሱም በእነዚህ ታጅቦ ከሰማይ ይወርዳል፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህን ጻፍ፤ “ከእንግዲህ ወዲህ የጌታ ኢየሱስ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው!” መንፈስ ቅዱስም “አዎ! ከድካማቸው እንዲያርፉ ሥራቸው ይከተላቸዋል” ይላል።