ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
1 ቆሮንቶስ 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሁሉ ነገር እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፤ የተጻፈው ግን በዘመናት መጨረሻ ለምንገኘው ለእኛ ተግሣጽ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱን ያገኛቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለምንነሣው ለእኛ ትምህርትና ምክር ሊሆነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ። |
ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
“በኀይለኛ ቊጣዬ በእናንተ ላይ ፍርዴን ተግባራዊ አድርጌ በምቀጣችሁ ጊዜ በአካባቢአችሁ ለሚኖሩ ሕዝቦች የመሳለቂያ፥ የሽሙጥ፥ የማስጠንቀቂያ የድንጋጤ ምክንያት ትሆናላችሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል።
ወንድሞች ሆይ! እኔ የምላችሁ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ አጥሮአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያለችው ሚስት እንደሌለችው ሆኖ ይኑሩ። ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌሉአቸው ሆነው ይኑር።
እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ እኛ በማሰብ አይደለምን? የሚያርስ ገበሬ በተስፋ እንዲያርስ፥ የሚያበራይም በተስፋ እንዲያበራይ፥ በዚህ ዐይነት ሁሉም ድርሻውን እንዲያገኝ ይህ የተጻፈው በእርግጥ ስለ እኛ ነው።
ይህም ምሳሌ ነበር፤ እነዚህ ሁለት ሴቶች የሁለት ኪዳኖች ምሳሌ ነበሩ፤ ከሲና ተራራ የሆነችው የአንደኛዋ ምሳሌ አጋር ናት፤ እርስዋ ልጆችን የምትወልደው ለባርነት ነበር።
ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።
ልጆቼ ሆይ! ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል” ሲባል ሰምታችኋል፤ እነሆ፥ አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ በዚህ ምክንያት የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን።