ግንበኞቹም የጌታን መቅደስ መሠረቱ፤ ካህናቱ ሙሉ ልብስ ለብሰው፥ መለከት ይዘው፥ የአሳፍ ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት መመሪያ መሠረት ጌታን እንዲያመሰግኑ መረጧቸው።
ዘካርያስ 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ እርሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል” ብሎ ነገረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ታላቅ ተራራ ሆይ፤ አንተ ምንድን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች፣ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ፣ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ተራራ በፊትህ የተደቀነው መሰናክል ሁሉ ይወገዳል፤ ቤተ መቅደሱንም መልሰህ ትሠራለህ፤ የመደምደሚያውንም ድንጋይ በስፍራው መልሰህ በምታኖርበት ጊዜ ሕዝቡ ‘እንዴት ውብ ነው! ውብ ነው!’ እያሉ የደስታ ድምፅ ያሰማሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፣ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፥ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ። |
ግንበኞቹም የጌታን መቅደስ መሠረቱ፤ ካህናቱ ሙሉ ልብስ ለብሰው፥ መለከት ይዘው፥ የአሳፍ ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት መመሪያ መሠረት ጌታን እንዲያመሰግኑ መረጧቸው።
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ “የሚያምን አያፍርም።”
እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።
አንተ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ አጥፊው ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እጄንም እዘረጋብሃለሁ፥ ከዓለትም ራስ ላይ አንከባልልሃለሁ፥ የተቃጠለም ተራራ አደርግሃለሁ።
እንዲህም ይሆናል፥ በመጨረሻው ዘመን የጌታ ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶች በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
ቆመ፥ ምድርንም አንቀጠቀጣት፥ ተመለከተ፥ ሕዝቦችንም አስደነገጠ፥ የዘለዓለም ተራሮች ተናጉ፥ የጥንት ኮረብቶች አጎነበሱ፥ የጥንት መንገዶች የእርሱ ናቸው።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ፥ በበለሲቱ ዛፍ እንደተደረገው ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሕፍት አላነበባችሁምን?
እርሱ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ “እንግዲህ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ ነው የማዕዘን ራስ የሆነው፤’ ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት ነው?