ሰሎሞን በኖረበት ዘመን ሁሉ ሃዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ሆነ። ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ።
ዘካርያስ 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንድ ወር ጊዜም እኔንም ስለሰለቹኝ፥ እነርሱም ስለጠሉኝ፥ ሦስቱን እረኞች አስወገድኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ። በጎቹ ጠሉኝ፤ እኔም፣ ሰለቸኋቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስቱ እረኞች እኔን ስላስቈጡኝና ስለ ጠሉኝ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስወገድኳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፣ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፥ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች። |
ሰሎሞን በኖረበት ዘመን ሁሉ ሃዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ሆነ። ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ።
የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’
አንቺ ባሏንና ልጆችዋን የጠላች የእናትሽ ልጅ ነሽ፥ አንቺም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የጠሉ የእኅቶችሽ እኅት ነሽ፥ እናታችሁ ኬጢያዊት ነበረች አባታችሁም አሞራዊ ነበረ።
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ሳሉ ጠላኋቸው፤ ስለ ሥራዎቻቸውም ክፋት ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።
የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
በዚህ ነገር ሁሉ ግን እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ ፈጽሞ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም።