ዘካርያስ 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋልና አልቅሱ! እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና አልቅሱ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጥድ ዛፍ ሆይ፤ ዝግባ ወድቋልና አልቅስ፤ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋል! የባሳን ወርካዎች ሆይ፤ አልቅሱ፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯል! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሊባኖስ ዛፎች ስለ ወደቁ፥ እናንተ የዝግባ ዛፎች “ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ፤ ግርማ የነበራቸው ዛፎች ሁሉ ጠፍተዋል፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ስለ ተቈረጠ የባሳን ወርካዎች “ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፣ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፥ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ። |