ከሠሯቸው ሥውር በደሎች ጋር ሳይታዩ ለማምለጥ ቢያስቡም፤ ጥቁሩ ዝንጉነት ጋርዷቸው፥ በጣረ ሞት ተሳቅቀው፥ በአስፈሪ ተስፋ መቁረጥ ተበታተኑ።
የበደሉትንም ዐስበው በውስጡ ብርሃን በሌለበት ቤት ውስጥ ከዝንጋዔ መጋረጃ በታች ተሰወሩ፥ እጅግም እየተደነቁ በድንጋጤ ቀለጡ፥ በምትሀትም ታወኩ።