ውርጭና ብርድ እሳቱን ተቋቁመው፥ ሳይሟሙ ቀሩ፤ ይህ የሆነው የጠላቶቻቸውን መክር ለማጥፋት፥ እሳት በበረዶ ውስጥ እንደሚነድ፥ በዝናብም ውስጥ ቦግ ብሎ እንደሚቀጣጠል ለእነርሱ ለማሳየት ነው፤
በረድና ውርጭ ከእሳት ጋር ጸንተው ቆሙ፤ እሳቲቱ በበረዱ መካከል እየነደደች፥ በዝናሞችም መካከል ቦግ ቦግ እያለች፥ የጠላቶችን አዝመራ ፍሬ እንዳጠፋች ያውቁ ዘንድ አልቀለጡም።