እነርሱ ስለ እግዚአብሔር ያላቸው የተሳሳተ አመለካከት ይኸው ብቻ አልነበረም፤ አላዋቂነት የወለደውን አስፈሪ የፍልሚያ ሕይወት እየመሩ፥ መቅሰፍቶቹን ሰላም ብሎ ይጠሯቸዋል።
ዳግመኛም እግዚአብሔርን ካለማወቃቸው የተነሣ ስሕተታቸው አልበቃቸውም፥ ነገር ግን በታላቅ ሰልፍ ሳሉ በስንፍናቸው ይኖራሉ። ይህን ያህል ክፉ የሆነውንም ታላቅ አደረጉ፥ ሰላም ብለውም ጠሩት።