ቀስ በቀስም አጥፊዎችን ታርማለህ፥ ኃጢአታቸውን ታስታውሳቸዋለህ፥ ትገስጻቸዋለህም፤ ጌታ ሆይ ይህንንም ያደረግኸው ከክፋት እንዲርቁና ባንተም ያምኑ ዘንድ ነው።
ስለዚህም የተሰነካከሉትን ሰዎች ለፍርድ እንዲመች ጥቂት በጥቂት ትዘልፋቸዋለህ፤ የበደሉትንም በደል ታሳስባቸዋለህ፤ ከክፋታቸውም ርቀው ኀጢአታቸውን በተረዱ ጊዜ አቤቱ፥ ያምኑብህ ዘንድ ትገሥጻቸዋለህ።