Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ጥበብ 12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሕያው የሆነው መንፈስህ በሁሉም ነገር ውስጥ ወርዷል!

2 ቀስ በቀስም አጥፊዎችን ታርማለህ፥ ኃጢአታቸውን ታስታውሳቸዋለህ፥ ትገስጻቸዋለህም፤ ጌታ ሆይ ይህንንም ያደረግኸው ከክፋት እንዲርቁና ባንተም ያምኑ ዘንድ ነው።


እግዚአብሔር በከነዓናውያን ላይ ያሳየው ትዕግስት

3 በቅድስት መሬትህ ላይ የነበሩትን የቀደሙ ሰፋሪዎች

4 በሥራዎቻቸው አስጸያፊነት ጠላሃቸው፤ ያልተቀደሱ ስርዓቶቻቸውንና አስማቶቻቸውን አልወደድህም።

5 ሕፃናትን የሚገድሉ ምሕረት የለሾች፥ በበዓላት ላይ የሰውን ስጋና ደም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚበሉ ሰው በላዎች፥ የምሥጢራዊ ወንድማማችነት ምልምሎች፥

6 እኒያ ራሳቸውን ማዳን የማይችሉ ሕፃናትን የሚገድሉ ወላጆች፥ በአባቶቻችን እጅ ይጠፉ ዘንድ ፈረድህ፤

7 ከሁሉም በላይ የምትወዳት ይህች መሬትም የእግዚአብሔርን ልጆች ታስተናግድ ዘንድ ፈቀድህ።

8 እነኚህንም እንኳ ሰዎች በመሆናቸው ራራኽላቸው፤ ከሠራዊትህ ፊት ፊት ተርቦችን በመላክ ጥቂት በጥቂት አጠፋሃቸው።

9 በተፋፋመ ጦርነት መሀል ክፉዎችን በጻድቃኖች እጅ መጣል ችግርህ አልነበረም፤ ወይንም እነርሱን በአስፈሪ አውሬዎች አልያም በቁጣ ቃል ልታጠፋቸውም በቻልህ ነበር፤

10 ምንም እንኳ እነርሱ በክፋት የተጠነሰሱ መሆናቸውን ብታውቅም፥ በተፈጥሮአቸው ክፉዎች ቢሆኑም፥

11 ከመጀመሪያው የተረገሙ ዘሮች መሆናቸው ሐሳባቸውን እንደማይሽሩ ብትገነዘብም፥ ፍርድህን ቀስ በቀስ በማሳየት ይጸጸቱ ዘንድ እድል ሰጥተሃቸዋል፤ ስለ ኃጢአታቸው ያልቀጣሃቸው ማንንም ፈርተህ አልነበረም።


የእግዚአብሔር ቻይነት ሲብራራ

12 ያደረግኸው ምንድነው? በማለት ሊጠይቅህ የሚደፍር፥ ፍርድህንም የሚቃወም የለምና። የፈጠርኻቸውን ሕዝቦች ብትደመስስ ከሳሽህ ከቶ ማነው? ክፉዎችን በመደገፍ አንተን የማጋፈጥ ይኖራልን?

13 ካንተ በላይ ስለ ሁሉም የሚጨነቅ፥ ፍርድህም ትክክለኛ እንደሆነ የምታረጋግጥለት፥ ሌላ አምላክ የለም።

14 ንጉሥም ቢሆን ፈላጭ ቆራጭ፤ ብይንህን ስላሳለፍክባቸው ሰዎች ደፍሮ ሊናገርህ አይችልም።

15 አንተ ትክክለኛ በመሆንህ፥ ዓለምን በፍትህ ታስተዳድራለች፤ በንጹሐን ላይ ቅጣትና ፍርድ፥ ከኃያልነትህ ጋር የማይሄድ ሆኖ ታየዋለህ።

16 ኃያልነትህ አዳኝነትህ፥ ልዕልናህ ምሕረትህ ያጐናጽፋሉና፤

17 ፍጹማዊ ሥልጣንህን ሰዎች ላለማመን ሲዳዳቸው፥ አውቀው የሚደፍሩትንም ግራ አጋባቸው።

18 አንተ ግን ኃይልህን ተቆጣጥረህ፥ ፍርድህን ሚዛናዊ አድርገህ፥ ከታላቅ ምሕረት ጋር ታስተዳድረናለህ፤ አንተ ከፈቀድህ ሥልጣኑ በእጅህ ነውና።


እግዚአብሔር ለእስራኤል የጠው ትምህርት

19 እንዲህ በማድረግህ ሕዝብህን አስተማርህ፤ ጻድቅ ሰው ለሌሎች ደግ መሆን እንዳለበት ገለጽህ፤ ለልጆችህ መልካም ተስፋን፥ ለኃጢአታቸውም ንስሐን ሰጠሃቸው።

20 ሞት የተፈረደባቸው ቢሆንም እንኳ፥ የልጆችህን ጠላቶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታና በላላ መልክ ከቀጣህ፥ ከክፋትም ይርቁ ዘንድ ጊዜና ቦታን ከሰጠሃቸው፥

21 ለአባቶቻቸው በመሐላ፥ በቃል ኪዳንና በተስፋ ቃል የገባህላቸውን ሰዎች ዘሮችና ያንተን ልጆች ትክክለኛውን ትኩረት ሰጥተህ ያልፈረድከው ስለምንድን ነው?

22 ስለዚህ በጠላቶቻችን ላይ ቅጣትህን ባለማክበድህ፥ እኛም በፍርዳችን ላይ ያንተን ደግነት እናስብ ዘንደ አስተማርኸን፤ ለፍርድም በቀረብን ጊዜ ምሕረትህን እንጠባበቃለን።


ደረጃ በደረጃ በግብጻውያን ላይ የወረደው ቅጣት

23 ከንቱና ክፋት የተሞላበት ሕይወት የሚመሩ ሰዎች በገዛ ራሳቸው መጥፎ ተግባር እንዲሠቃዩ ያደረግኸውም ለዚሁ ነው።

24 በስሕተት መንገድ ብዙ ተጉዘዋል፤ መርዘኞቹንና የጠሉትን እንስሳት በማምለክ፥ ክፉና ደጉን እንዳልለዩ ለጋ ሕፃናትም ታልለዋልና።

25 አንተም ምንም እንደማያውቁ ሕፃናት የሰው መሳቂያ በማድረግ ቀጣሃቸው።

26 ከተሳልቆው ተግሣጽ ያልተማሩ ግን የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍርድ በቶሎ ይቀበላሉ።

27 እነርሱን ያሰቃያቸው፥ አቤቱታቸውን ያቀረቡባቸው፥ አምላኮቻቸው ያደረጉአቸው እነኛው ፍጡራን፥ የቀጧቸውም እነርሱ መሆናቸውን በእውነተኛው ብርሃናቸው ተመልክተዋል፤ እስከ አሁን ድረስ አናውቅህም ያሉትን ጌታ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ አወቁ፤ የመጨረሻውም ቅጣት በእነርሱ ላይ ወደቀ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos