ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
ማሕልየ መሓልይ 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉንጩና ጉንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣ የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ ውብ አበቦች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጉንጮቹ ማማር ጣፋጭ ሽታ ያላቸው የቅመማቅመም ዕፀዋት እንደሚገኙበት የአትክልት ቦታ ነው፤ ከንፈሮቹ መዓዛው የሚጣፍጥ የከርቤ ሽቶ እንደሚያፈሱ የአሸንድዬ አበባዎች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕንጮቹ ሽቱን የሚያፈስሱ የሽቱ መደብ ናቸው። ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠባጥባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕንጩና ጕንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ። |
ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።