ማሕልየ መሓልይ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፥ ጸጉሩ የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራም ጥቁር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱ የጠራ ወርቅ፣ ጠጕሩ ዞማ፣ እንደ ቍራም የጠቈረ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ራስ የወርቅ ሉል ይመስላል፤ ጠጒሩም ዞማና እንደ ቊራ የጠቆረ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፤ ቈንዳላው የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቍራ ጥቍረትም ጥቁር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፥ ቈንዳላው የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራ ጥቁረትም ጥቁር ነው። |
እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።