ሩት 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ሕይወትሽን ያድሳታል፤ በእርጅና ዘመንሽም ይጦርሻል፤ የምትወድድሽና ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ ወልዳዋለችና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፤ በእርጅናሽም ይመገባሻል፤” አሉአት። |
እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻችኋለሁ እኔም አነሣችኋለሁ፤ እኔ እሸከማችኋለሁ እኔም አድናችኋለሁ።
ባሏ ሕልቃናም እርሷን፥ “ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር።
ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል። መካኒቱ ሰባት ወለደች፥ ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች።