ሮሜ 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ውስጥ ከአይሁድ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ደግሞ እኛን ጠራን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠራው ከአይሁድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ወገን የሆንነውን እኛን እንኳ ሳይቀር አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛን የምሕረት ዕቃዎቹንም ከአይሁድ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም ጠርቶናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ክብሩ የጠራንና የሰበሰበንም እና ነን፤ ነገር ግን ከአሕዛብም ነው እንጂ ከአይሁድ ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን። |
በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።
በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ እርሱ ራሱ ያበረታችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ያቆማችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።