ሮሜ 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ የፈለገውን ይምረዋል የፈለገውንም እልከኛ ያደርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወድደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነድነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይምረዋል፤ የሚፈልገውንም እልኸኛ ያደርገዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የሚወድደውን ይምረዋል፤ የሚወድደውንም ልቡን ያጸናዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል። |
እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፥ እርሱም ያሳድዳቸዋል፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ ላይ ክብር አገኛለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።
ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።
ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤
“የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።”
ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ፥ እንዲያጠፉአቸው ምሕረትንም ሳያደርጉ ፈጽመው እንዲፈጅዋቸው፥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ልባቸውን እንዲያደነድኑ ከጌታ ዘንድ ሆነ።