ሮሜ 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋራ ሆኖ ይመሰክርልናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኛ መንፈስ ጋር ሆኖ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለእኛ ይመሰክራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እና የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆን ለልቡናችን ምስክሩ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። |
ፍጥረት ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን እኛ ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት በናፍቆት እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።
እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሁ፥ በክርስቶስም አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፤ እንዲሁም ነን። ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛንም አያውቀንም።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በራሱ ምስክር አለው፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።