Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 8:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ፍጥረት ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን እኛ ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት በናፍቆት እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እርሱ ብቻ ሳይሆን፣ የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ ያገኘን እኛ ራሳችን የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነታችንን በናፍቆት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ነገር ግን በመቃተት ላይ ያለው ፍጥረት ብቻ አይደለም፤ የመጀመሪያውን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ የተቀበልን እኛም የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን በተስፋ እየተጠባበቅን በውስጣዊ ሰውነታችን በመቃተት ላይ እንገኛለን፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ነገር ግን የሚ​ተ​ክዝ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ የተ​ቀ​በ​ል​ነው እናም ደግሞ እና​ዝ​ና​ለን እንጂ፤ የነ​ፍ​ሳ​ች​ንን ድኅ​ነት እና​ገኝ ዘንድ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንና፤ በእ​ም​ነ​ትም ድነ​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 8:23
26 Referencias Cruzadas  

ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በብዛት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት በብዛት አቀረቡ።


እንደ መላእክት ናቸውና፥ ወደ ፊት ሊሞቱም አይችሉም፤ የትንሣኤም ልጆች እንደመሆናቸው መጠን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።


ይህም መሆን ሲጀምር መዳናችሁ ቀርቦአልና ቁሙ፤ ቀናም በሉ።”


ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።


በዚህ ብቻ ሳይሆን፥ መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ ስለምናውቅ በመከራም ጭምር እንመካለን፤


ተስፋም ቅር አያሰኘንም፤ ምክንያቱም በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ነው።


እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?


ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃልና።


እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ፥ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤


ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።


ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።


እኛ በመንፈስ፥ በእምነት፥ የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና።


እርሱም ለክብሩ ምስጋና ለእግዚአብሔር ሕዝብ ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ የርስታችን መያዣ ነው።


ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።


የብርሃን ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና፤


ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።


እንዲሁም የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድንጠብቅ ያስተምረናል፤


እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos