ሮሜ 6:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእርሱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር አንድ ከሆንን እንዲሁም ደግሞ በትንሣኤው ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞቱ ከርሱ ጋራ እንደዚህ ከተዋሐድን፣ በትንሣኤው ደግሞ በርግጥ ከርሱ ጋራ እንተባበራለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሞቱ ከእርሱ ጋር እንዲህ አንድ ከሆንን እንዲሁ በትንሣኤው ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞቱ ከመሰልነውም በትንሣኤው እንመስለዋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤ |
መሬቱን ቈፈረ፤ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤ የወይን መጭመቂያ ጉድጓድም አበጀ፤ ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።
እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?