Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እርሱ ግን መልሶ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እርሱ ግን መልሶ፦ የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 15:13
11 Referencias Cruzadas  

በእኔ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እንድከብር የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘለዓለም ይወርሳሉ።


በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል፤ ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፤ ያቃጥሉአቸውማል።


ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።


ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።


በዚያን ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ቀርበው “ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ ታውቃለህን?” አሉት።


“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።


እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios