በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።
ሮሜ 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፤ ለራሱም የሚሞት የለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኛ ማንም ለራሱ የሚኖር፣ ለራሱም የሚሞት የለምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኛ እያንዳንዱ ሕይወቱም ሆነ ሞቱ የራሱ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመካከላችንም ለራሱ የሚኖር፥ ለራሱም የሚሞት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤ |
በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።
ይህንን ተረድቼአለሁ፤ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ገዢዎችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።